top of page

ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛል

1ኛ ቆሮ 16፤9

በመካከለኛው የካልፎርንያ ግዛት የተቋቋመው የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገዳም በአጭር ግዜ የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል።

 

ይህም በዚህ አገር ተወልደው ለሚያድጉ ልጆች ልዩ ትኩረት ማድረግን መሰረት ያደረገ እንዲሁም አፋጣኝ ድጋፍ ለሚሹ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን አስቸኳይና የተሟላ አግልግሎት ለመስጠት ይቻል ዘንድ አማራጭ ሀሳብን ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንገኛለን። የገዳሙን አገልግሎት በተለየ ሁኔታ ለልጆችና ለወጣቶች ተደራሽ ለማድረግ የምዕመናንን አስቸካይ ድጋፍ መጠይቅ ግድ ብሏል። በመሆኑም አቅማችሁ የሚፈቅድ እያንዳንዳችሁ የ$5,000 ወይንም አቅማችሁ የፈቀደውን መጠን ብድር ለገዳሙ በመስጠት ይህን ትልቅ ዕራዕይ እውን ለማድረግ ትረባረቡልን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናቀርባለን።  ለዚህ ታላቅ አገልግሎትና አላማ የሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆናችሁ ሁሉ አሻራቸውን በማስቀመጥ በታሪክ እና በትውልድ የማይረሳ ሕያው የሆነ ሥራ እንድትሠሩ እናሳስባለን።

በዚህ ታላቅ ተግባር ለመሳተፈና በረከት ለማግኘት ከታች ባለው ቅፅ ላይ ስጦታዎን ወይም በብድር ለመስጠት ያሰቡትን ያስፍሩ።

bottom of page