top of page

የኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳም ድጋፍ ሰጪ ማሕበራት አላማ አጭር ማብራሪያ

ጥንታዊት፤ ሐዋርያዊት፤ ዓለም አቀፋዊት፤ ታሪካዊትና ብሔራዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አሁን በአለንበት የ21ኛው ክፍለ ዘመን በአገር ውስጥና በውጭ ዓለም ለሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች “በአማኑኤል፤በአለ ወልድ፤ መድኃኔዓለም፤ ቅድስት ድንግል ማርያም፤ ቅዱሳን መላእክት፤ ጻድቃንና ሰማእታት ስም ማሕበራት በማቋቋም የምትሰጠው መንፈሳዊና ማኅበራዊ አግልግሎት ዘመን ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ከሐዋርያት የተረከበችውን እምነት፤ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፤ አስተምህሮና ትውፊት በመጠበቅና በማስጠበቅ እንዲሁም ሁሉንም የሰው ልጅ በእኩልነት፤በፍቅር፤ በአንድነትና በሰላም በመያዝ ለትውልድ የሚተላለፉ በርካታ ሥስራዎችን እንዳከናወነችና በማከናወን ላይም እንዳለች በሁሉም ዘንድ የማይካድ ሐቅ ነው።

$5/Month X 12=$60/year

$10/Month X 12=$120/year

Custom Amounts

በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወይንም ቅድስት አርሴማ ስም “የኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳም ድጋፍ ሰጪ ማሕበራትን፤ ማቋቋም የተፈለገበት ዋና አላማና ምክንያትም፤

 1. በትንሽ ስጦታ ገዳሙን በቋሚነት በመርዳት የእግዚአብሔርን ስጦታዎች ለመቀበል እንዲቻል፤ (“ስጡ ይሰጣችሁማል”ሉቃ6:38)

 2. እግዚአብሔር በገባላቸው ቃል ኪዳን መሠረት ከመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወይንም ቅድስት አርሴማ በረከት ለማግኘት፤ (“ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል” ማቴ10:41

 3. ምእመናንና ምእመናት የበለጠ የመንፈስ አንድነት እንዲኖራችው ላማድረግ ነው።(“በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ” ኤፌ2:22

ስለሆነም በመካከለኛው የካልፎርንያ ግዛት ሳን ሚግየል ከተማ፤ ሞንተረይ ካውንቲ የተቋቋመው የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአንድነት ገዳምን መንፈሳዊና ማሕበራዊ አገልግሎት ለማስፋፋት በቋሚነት ሊሠሩ ከታቀዱ ሥራዎች መካከል ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ዋና ሥራ አንዱ በዚህ አገር ተወልደው በማደግ ላይ ለሚገኙ ልጆቻችን እና በልዩ ልዩ ችግሮች ለሚሰቃዩ እና እርዳት ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን አስቸኳይና የተሟላ አግልግሎት መስጠት የሚቻልበትን ቅድመ ሁኔታዎች በማዘጋጀት በተግባር ላይ ማዋል የኆኅተ ሰማይ ገዳም ዋና አላማና ራእይ መሆኑ አያጠያይቅም።

ስለዚህ በኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አንድነት ገዳም የሚሰጠው መንፈሳዊና ማሕበራዊ አገልግሎት የተሳለጠ ይሆን ዘንድ ሁሉም የሚችለውን አምስት ወይንም አሥር ዶላር በወር በቋሚነት በመስጠት የበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችል“የኆኅተ ሰማይ ገዳም ድጋፍ ሰጪ ማሕበራት” በሚል ስያሜ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት አርሴማ ስም ማሕበር ተቋቁሟል። ስለሆነም ከዚህ በታች ያለውን ፎርም በመሙላት የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወይንም ቅድስት አርሴማ ማሕበርተኛ በመሆን የገዳሙን አገልግሎት እንዲደግፉ በአክብሮት እንጠይቃለን።

 

“እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም” ኤፌ 2:19

bottom of page