top of page
  • Facebook

ለጉብኝት፤ ለጸበል፤ ለሱባኤ፤ ለመንፈሳዊና መሕበራዊ አገልግሎት ለሚመጡ እንግዶች የተዘጋጀ መመሪያ/አስገዳጅ ሕግ 


1. የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳምን ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶች ከሰባት ቀናት በፊት አስቀድመው በገዳሙ ዌብ ሳይት ላይ የተለጠፈውን የእንግዳ መመዝገቢያ ፎርም (Online) ቅጽ መሙላት ግዴታ አለባቸው። 

2.የእንግዳ መመዝገቢያ ፎርሙን ሳይሞሉና ሳይመዘገቡ ገዳሙን ለመጎብኘት የሚመጡ እግዶችን ከገዳሙ ውስጥ ለማሳደርና ገዳሙን ለማስጎብኘት ፈጽሞ አይቻልም። 

3. የገዳሙን የእንግዶች መመዝገቢያ ፎርም/ቅጽ ሞልተው የላኩ እንግዶች በተሞላው ፎርም መሠረት ከመምጣታቸው በፊት በቂ የሱባኤ መያዛ ቦታ/ ማረፊያ መኖሩን የገዳሙ ኃላፊዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥና ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል። 

4. ለሱባኤ፤ለጸብልና መንፈሳዊና መሕበራዊ አገልግሎት ለማግኘት ለሚመጡ እንግዶች ማረፊያ/መቆያ የሚሰጣቸው አስቀድመው የመመዝገቢያ ፎርሙን ለሞሉ ብቻ ይሆናል። 

5.ወደኆኅተሰማይአንድነትገዳምመንፈሳዊናመሕበራዊአገልግሎትለማግኘትናሱባኤለመግባትየሚመጡ እንግዶቻችን ከገዳሙ በር ላይ ሲደርሱ በሩን ለማስከፈት ስልክ መደወል አለባቸው። 

6. ወደ ኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳም አገልግሎት ለማግኘት፤ ሱባኤ ለመግባትና ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶቻችን ከገዳሙ በር ላይ ሲደርሱ ስልካቸውን ከመኪና ውስጥ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።ማንኛውም ሰው የኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳምን ለመጎብኘትና በገዳሙ ውስጥ የሚመጣ ከገዳሙ ግቢ ውስጥ ስልክ መደወል፤ ሙዚቃም ሆነ ዜና መስማት፤ የተለያዩ የሶሻል ሚድያዎችን መጠቀም ሆነ ማየት ፈጽሞ የተከለከለ ነው። 

7.ወደኆኅተሰማይአንድነትገዳምአገልግሎትለማግኘት፤ሱባኤለመግባትናለመጎብኘትየሚመጡእንግዶቻችን የተጠቀመበትን እቃ ከቆሻሻ ማስቀመጫው ውስጥ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። 

8. በኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳም ውስጥ የሱባኤ ጊዜ የሚያሳልፉ እንግዶች የማረፊያ ክፍላቸውን በጽዳት መያዝ፤ መብራቱን በሰዓቱ ማብራትና ማጥፋት፤ጫማቸውን ከበር አውልቀው ማስቀመጥና የተረፉ ምግቦችን ከቆሻሻው ማስቀመጫ ወስደው ማስቀመጥ ሙሉ ኃላፊነት አለባቸው። 

9. በኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳም ውስጥ በእንግድነት የሚቆዩ እንግዶቻችን በሚቆዩበት ጊዜ የጠፋ፤የተሰበረና የተበላሸ እቃ ከተገኘ የማሠራት ወይም የመተካት ግዴታ አለባቸው። 

10. በኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳም ውስጥ ለሱባኤም ሆነ ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚመጡ እንግዶቻቸን የሚቆዩበትን ቦታ ቁልፍ ሲረከቡ በቤቱ ውስጥ ያሉትን እቃዎች፤ የቤቱን ጽዳትና የሚያስፈልጉ እቃዎችን አይተው መረከብ አለባቸው።በመጨረሻም ገዳሙን ለቀው በሚወጡበት ጊዜ አጽድተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል። የሰነበቱበትን ቤት ሳያጸዱ የሚሄዱ ለጽዳት ሠራተኛ ገንዝብ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። 

11. ወደ ኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳም አገልግሎት ለማግኘትና ሱባኤ ለመግባት የሚመጡ እንግዶቻችን ድምጻቸውን በመቀነስ ጸጽታ የሰፈነበት የጸሎትና የሱባኤ ጊዜ ለማሳልፍ እንዲችሉ የሚሰጣቸውን መመሪያ መከተል አለባቸው።

12. ወደ ኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳም አገልግሎት ለማግኘትና ሱባኤ ለመግባት የሚመጡ እንግዶቻችን ከቤተ ሰበእ ጋር ለመገናኘትም ሆነ ለሚፈልጉት ጥያቄ በማደሪያ ክፍሎች የሚገኙትን የገዳሙ ስልኮች መጠቀም ይችላሉ። 

13. ወደ ኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳም አገልግሎት ለማግኘት፤ ሱባኤ ለመግባትና ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶቻችን የእራሳቸውን ለምኝታ የሚጠቀሙባቸውን አንሶላ፤ስሊፒንግ ባግ፤ፎጣና ለእራሳቸው የሚመገቧቸውን የምግብ አይነቶችን ይዘው መምጣት አለባቸው። 

14. ለሱባኤና ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚመጡ እንግዶች ወደ ገዳሙ የአልኮል መጠጦችንና ያልተፈቀዱ ምግቦችን ይዞ መግባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው። 

15. ሱባኤ ለመግባት በገዳሙ ድረ ገፅ (Website) ፎርም ሞልተው ሲመጡ በተፈቀደላቸው የሱባኤ ወቅት የሚገለገሉባቸውን ሀ/ የገዳሙን ሥርዓት የማይቃረኑ ምግቦችና የመሬት ፍራሽ ለ/ አንሶላ፣ ነጠላ ጫማ እንዲሁም ኮምፎርት (ብርድ ልብስ) ይዘው የመምጣት ግዴታ አለባቸው። 

16. ለወደፉቱ የጋራ መመገቢያ አዳራሽ እስከሚሠራ ድረስ ለጊዜው ሁሉም በየክፍላቸው መመገብ ይችላሉ። 

17. በኆኅተ ሰማይ ገዳም ውስጥ ለሱባኤ፤ለጉብኝት አገልግሎት ለማግኘትና ለጸበል የሚመጡ እንግዶች ሁሉም በገዳሙ ሥርአት መሠረት በቀን አንድ ጊዜ ብቻ በዘጠኝ ሰዓት ይመገባሉ። 

18. በኆኅተ ሰማ የአንድነት ገዳም ውስጥ በኗሪነት የሚቀመጡ መነኮሳትና መነኮሳይት እንዲሁም በጊዜአዊነት የሚቆዩ እንግዶች የሚመገቧቸው የምግብ አይነቶች ዳቤ፤ጥራጥሬ፤ንፍሮ፤እንጀራና አንድ አየነት ወጥ ብቻ ይሆናሉ። 

19. የልደት፤የጥምቀት፤የትንሣኤ፤ የጰራቅሊጦስ፤ሐምሌ አምስት ቀንና ነሐሴ አሥራ ስድስት ቀን የኪዳነ ምሕረት ካልሆነ በስተቀር የሥጋ አይነት ምግቦችን በገዳሙ ውስጥ መመገብ አይፈቀድላቸውም። 

20. የኆኅተ ሰማይ አንድነት ገዳምን ለመጉብኝት፤ለሱባኤ፤ ለመንፈሳዊና መሕበራዊ አገልግሎት ለሚመጡ እንግዶች ለጊዜው ምንም ዓይነት ምግብና መጠጥ በማቅረብ ማስተናገድ የማይቻል መሆኑን በቅድሚያ በአክብሮት እንገልጻለን። 

21. በኆኅተ ሰማይ የአንድንት ገዳም ውስጥ ሱባኤ የያዙ እንግዶች ከተሰጣቸው ማረፊያ ውጭ በገዳሙ የሥራ ኃላፊዎች ካልታዘዙ በስተቀር ወደ ሌሎች ማረፊያ ቦታዎች መሄድ አይፈቀድላቸውም። 

22. ከአሥራስምንት ዓመታት በታች ያሉ ልጆጆች ለጉብኘት ወደ ገዳሙ በሚመጡበት ጊዜ በኃላፊነት የሚጠብቅ አዋቂ ሰው መኖር ግዴታ ነው። 

23. ወደ ኆኅተ ሰማይ የአንድነት ገዳም የሚመጡ እንግዶች ለማዳ እንስሳትን ማለት ድመትና ውሻን ይዘው መምጣት አይፈቀድላቸውም። 

24. በኆኅተ ሰማይ የአንድነት ገዳም ውስጥ የሚቆዩ እንግዶች ከጸብ፣ ከክርክር፣ ከጩኸት፤ ከአላስፈላጊ ንግግር ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎችን ሕገ ወጥ ተግባራት የሚፈጽሙ እንግዶች የመጡበትን የስባኤ ጊዜ ሳይጨርሱ አቋርጠው ከገዳሙ እንዲወጡ በሕግ ይገደዳሉ። 

25. በኆኅተ ሰማይ ገዳም ውስጥ ለሱባኤ፤ለጸበል፤ለመንፈሳዊና መሕበራዊ አገልግሎት የሚሜጡ እንግዶች በገዳሙ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ ተገቢውን ጥንቃቄ በለማድረግ ለሚደርስባቸው ማንኛውም አደጋ ኃላፊነቱ የእራሳቸው ብቻ ሲሆን ገዳሙ በኃላፊነት በሕግ የማይጠየቅ መሆኑን በቅድሚያ እናሳስባለን። 

26. ምንም ዓይነት ፈቃድ ሳይሰጠው የገዳሙን ንብረት ለገዳሙ ሥራ ካልሆነ በስተቀር ለግል ዓላማው መጠቀምም ሆነ ወደ ቤቱ መውሰድ አጥብቆ የተከለከለ ሲሆን (ወንጀልም ነው) በመጽሐፍ ቅዱስ ኢታንስዕ ዘኢያንበርከ (ያላስቀመጥከውን አታንሣ) ይላልና ኃጢአትም ነው። 

27. በገዳሙ ውስጥ የሚቆዩ እንግዶቻችን በማኅበርም ሆነ በተናጠል የሚሠሩ የጉልበት፤የእውቀት፣ የገንዘብ እና የቁሳቁስ እርዳታዎችን በማድረግና አስፈላጊውን ሥራ በመሥራት የገዳሙን መንፈሳዊና ማሕበራዊ አገልግሎት ማስፋፋት ይጠበቅባቸዋል።

 

28. ለገዳሙ በቋሚነት ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀውን የመመዝገቢያ ቅጽ/ ፎርም በመሙላትና በመመዝገብ ዓመታዊ ክፍያ በመፈፀም የገዳሙን መንፈሳዊና ማሕበራዊ አገልግሎት መደገፍ አለባቸው። 

29. ለሱባኤ ወደ ገዳሙ የሚመጡ እንግዶች በሱባኤ ወቅት ከአልጋ ላይ መተኛት ስለማይፈቀድ በሚሰጣቸው የማረፊያ ቦታ ማረፍ ግዴታ አለባቸው፤ 

30. በገዳሙ ማረፊያ ቤት ለሱባኤ በሚቆዩበት ጊዜ የገዳሙን ወጪ ለመቀነስ ገዳሙ በሚያወጣው ተመን መሠረት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ክፍያ መፈፀም አለባቸው። 

31. ወደ ኆኅተ ሰማይ የአንድነት ገዳም የሚመጡ እንግዶቻችን ከገዳሙ ውስጥ የሴትና የወንድ ማረፊያ የተለያየ በመሆኑ ከገዳሙ የሚሰጣቸውን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው። 

32. ወደ ኆኅተ ሰማይ የአንድነት ገዳም ለአገልግሎትና ለሱባኤ የሚመጡ እንግዶች ከገዳሙ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ በየቀኑ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጥር ማታና ጠዋት 11:00 ሰዓት (11:00am/5:00pm) ከቤተ ክርስቲያን በመገኘት የሰርክ ጸሎትና ጸሎተ ኪዳን ማስደረስ፤ የግል ጸሎት ማድረግና እንዲሁም የቅዳሴ አገልግሎት በሚኖርበት ጊዜ የማስቀደስ ግዴታ አለባቸው። 

33. ወደ ኆኅተ ሰማይ የአንድነት ገዳም መንፈሳዊና መሕበራዊ አገልግሎት ለማግኘትና ሱባኤ ለመግባት የሚመጡ እንግዶቻችን ለሚኖራቸው ማናቸውም ጥያቄዎች በሚከተሉት የስል ቁጥሮች በመደወል ለጥያቄያቸው አፋጣኝ መልስ ማግኘት እንደሚችሉ በአክብሮት እናሳስባለን።

 

ስልክ ቁጥሮች

805-643-2222

310-621-4588

720-755-6507

202-683-5791

bottom of page